InternationalNews

በሊቢያ የስደተኞች ህልፈት

በሊቢያ የባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ መስመጥ አደጋ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የ38 ስደተኞች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች ማንነት በመለየት ለቤተሰቦቻቸው ለማሳወቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጸው የሊቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ከዚሁ አደጋ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት ባላቸው ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ላይ ምርመራ መጀመሩንም አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጃ በአውሮፓውያኑ በ2026 በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሞቱና የጠፉ ስደተኞች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ መድረሱን ጠቁሟል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv