የነዳጅ አቅርቦት ውሳኔ
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የናፍጣ ነዳጅ የአቅርቦት መጠን ከዛሬ ጀምሮ ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ መወሰኑን ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።
ሚኒስትሩ ከጦርነቱ በኋላ የናፍጣ አቅርቦት በግማሽ ቀንሶ አቅርቦቱ ወደ 4.5 ሚሊየን ሊትር ዝቅ ብሎ እንደነበር አስታውሰው ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የናፍጣ አቅርቦት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት በቀን 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ሚኒስትሩ መንግስት በአጣዳፊ ግዥ የቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ በመግዛት ችግሩን መቋቋም አስችሏል ብለዋል።
ሚኒስትሩ መንግሥት ጦርነቱን ተከትሎ በወር እስከ 20 ቢሊዮን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ በመጥቀስ፤ አጠቃላይ የድጎማ ክምችቱ 300 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግረዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
