የአሜሪካ በየመን ስደተኞች ግድያ-የአምነስቲ ጥሪ
አለም አቀፉ የመብት ተሟጋች አምነስቲ በየመን በሚገኝ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች ስደተኞች ባሉበት አንድ ማረሚያ ቤት ላይ ከ9 ወራት በፊት በአሜሪካ የተፈፀመው የአየር ጥቃት እንዲጣራ ጠየቀ።
አሜሪካ የዛሬ አመት ገደማ በየመን በሚገኝ አንድ ማረሚያ ቤት ላይ በፈፀመችው ጥቃት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በትንሹ 68 ስደተኞች መሞታቸው እና 47 መቁሰላቸው ይታወሳል።
አምነስቲ አክሎም ጥቃቱ እንደ ጦር ወንጀል ተቆጥሮ ምርመራ እንዲካሄድበት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
በጥቃቱ ሳቢያ ስድስት ኢትዮጵያውያን ቆስለው እንደነበር እና ሁለቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ እነዚሁ ተጎጂዎች እስካሁን ምንም አይነት ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው ሲገለፅ አሜሪካ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ይፋ ያደረገችው ምርመራ እንደሌለ አልጀዚራ ዘግቧል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
