የአረብ ኤምሬትስ ውሳኔ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ ከነዳጅ ላኪዎች ሀገራት ድርጅት ወይም ኦፔክ አባልነቷ መውጣቷን አሳውቃለች።
በኢራን ጦርነት ምክንያት ዓለም አቀፍ የነዳጅ እጥረት ቀውስ በተፈጠረበት በዚህ ወቅት ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ መድረሷ ደግሞ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ በድርጅቱና በዓለም ገበያ ላይ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ከኦፔክ አባላት መካከል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አንዷ ግዙፍ ነዳጅ አምራች ሀገር መሆኗን ተከትሎ የሀገሪቱ ከአባልነት መውጣት ድርጅቱ በዓለምአቀፍ ደረጃ ያለውን የነዳጅ አቅርቦትና ዋጋ ትመና ላይ በመቆጣጠር ረገድ ያለው ሚና እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የተባባሩት አረብ ኤምሬትስ ከድርጅቱ መውጣቷን ተከትሎ በኦፔክ ሕግጋት የማትመራ በመሆኑ ለዓለም ገበያ የምታቀርበውን የነዳጅ ምርት መጠን ለማሳደግ ያግዛታል እየተባለ ይገኛል፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
