EthiopiaNews

የፕሬስ የቦርድ አመራሮች

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ጉባኤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራሮችን ሹመት መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

የሥራ አመራር ቦርድ አባላቱ የድርጅቱን ዓላማ ተገንዝበው ብቃት ያለው አመራር ለመስጠት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ለምድ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለድርጅቱ 9 አባላት ያሉት የቦርድ አመራሮች የተሸሙ ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢም ሆርን ሪቪው የተሰኘ መገናኛ ብዙሃንን ከጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ በስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተርነት ሲመሩ የቆዩ ብሌን ማሞ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

የምክር ቤት አባላትም የሹመት ስብጥሩ ብዝሃነትን ማዕከል ያደረገ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ለሀገር ዕድገት ትልቅ እስተዋፅኦ እያደረጉ ያሉ አመራሮች መሆናቸውና ተቋሙን ለመምራት ብቃት ያላቸው ተሿሚዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv