EthiopiaNews

85ኛው የድል በዓል

85ኛው የድል በዓል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት አደባባይ ዛሬ ማለዳ ተከብሯል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ ፤ ዕለቱ ፋሺዝምና ናዚዝም ድል የተመቱበት ታላቅ ቀን ነው ለመላው የሀገሪቱ ሕዝቦችና ለአርበኞች የእንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ ይህንን የድል በዓል የምታከብረው በአርበኞቿ ጽናትና በመራራ ተጋድሎ ነው፡፡

አርበኞች በባዶ እግራቸውን ዝናራቸውን ታጥቀው ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀን ወራሪ ኃይል ማሸነፋቸው የፋሺስት አስተሳሰብ ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎታልም ሲሉ ገልጽዋል፡፡

በዓሉን ለማክበር ከፕሬዝዳት ታዬ በተጨማሪ የጀግኖች አርበኞች ማኅበርን በመወከል የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ እንዲሁም የባህር ሃይል ቫይስ አድሚራሉ ክንዱ ገዙ ተገኝተዋል አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሃውልት ስርም የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በዓሉን በማስመልከት ባደረጉት ንግግድ ላይም የዛሬው ዘመን ትውልድ የአባቶቹን መታወሻ እና የታሪክ ቅርስ ከመዘከርና ከመጠበቅ ባሻገር ሌላ አዲስ የአርበኝነት እውድ ሊፈጥር እንደሚገባ ነው የተገለጸው፡፡

የትላንቱ አርበኝነት ሀገርን ከባዕድ ወራሪ ማዳን እንደነበር ኹሉ፣ የዛሬው አርበኝነት ደግሞ ሀገርን ከድህነት፣ ከኋላቀርነት እና ከተመጽዋችነት ማላቀቅ ነውም ተብሏል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews