የኮሚሽኑና ከትጥቅ ተመላሾች ውይይት
የኮሚሽኑና ከትጥቅ ተመላሾች ውይይትየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 200 ከሚደርሱ በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ ከቆዩ ዜጎች ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ በሌሎች አካባቢዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለማካተት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት በተደረገ ውይይት በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና ሰላምን መርጠው የተመለሱ አካላት 17 አጀንዳዎችን ሰንደው ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን ያስታወቁት ኮሚሽነሩ የተነሱ ጥያቄዎች ኮሚሽኑ ለሚመለከተው አካል ማቅረቡንም ተናግረዋል።
አክለውም ይህ መድረክ ከኮሚሽኑ ጋር ይበልጥ ተቀራርባችሁ ለሰላም የምትሰሩበት፣ የቀሩ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ምክረሃሳብ የምትሰነዝሩበት ይሆናልም ብለዋል።
የውይይጡ ተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር ምክክር የሀሳብ ልዩነቶችን የመፍቻ ብቸኛ መንገድ መሆኑን እንደሚያምኑ መናገራቸውንም ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
