የኢትዮጵያ ምላሽ ለሱዳን
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ ሱዳን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ እንዲሁም በጦሩ ቃል አቀባይ በኩል በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበችው ክስ መሰረተ ቢስ ክስ ነው ሲል አሳውቋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም የኢትዮጵያ መንግስት የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የረጅም ጊዜ ወንድማማችነትና ታሪካዊ ትስስር በማክበር፤ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ደህንነት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ይፋ ሳያደርግ በትዕግስት ማለፉን አስታውቋል።
ከጥሰቶች ውስጥ የህወሓት ቅጥረኞችን በሱዳን ጦርነት ውስጥ በስፋት ማሳተፍ አንዱ መሆኑንና ሀገሪቱ የተለያዩ ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች መናኸሪያ እየሆነች መምጣቷን የሚያሳዩ ተአማኒነት ያላቸው ማስረጃዎች መኖራቸውንም ጠቁሟል።
የሱዳን ጦር ለእነዚህ የህወሓት ቅጥረኞች የጦር መሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ድንበር በኩል ጥቃት እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
የሱዳን ጦር ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ላይ የሚያቀርቧቸው ክሶች የራሳቸውን አላማ ለማራመድ በሚንቀሳቀሱ የውጭ ኃይሎች ግፊትና ትዕዛዝ የሚፈጸሙ መሆናቸውንም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አብራርቷል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
