EthiopiaNews

የመሬት ጨረታዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተያዘው በጀት ዓመት በሦስት ዙር ባካሄዳቸው ግልጽ የመሬት ጨረታዎች ከ3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል።

ቢሮ ይህን ገቢ የሠበሠበው ከይገባኛል ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የጸዳ 9 ነጥብ 29 ሄክታር መሬት ወይም 328 ፕሎቶች ለጨረታ አሸናፊዎች በማስተላለፍ መኾኑን ገልጿል።

ቢሮው ለጨረታ ያቀረባቸው መሬቶች ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድ እና ለተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ እንደኾኑ አስታውቋል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተገኘ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv