InternationalNews

የዓለም የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ

የአሜሪካና ኢራን ግጭት በሆርሙዝ ሰርጥ ዳግም ማገርሸቱን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ እስከ 8 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተነገረ፡፡

ሁለቱ ሀገራት በሆርሙዝ ሰርጥ ዳግም ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ አንዳቸው ሌላኛቸውን ለግጭቱ ተጠያቂ በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን የዋሽንግተን አስተዳደር ምንም እንኳን ግጭቱ ቢከሰትም የተኩስ አቁም ስምምነቱ አሁንም እንደፀና መሆኑን አሳውቋል፡፡

የዓለም የነዳጅ መለኪያ የሆነው ብሬንት የኢራን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ እስከ 40 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማስመዝገቡ ሲነገር ዕለታዊ ምርቱም እስከ 15 ሚሊዮን በርሜል መቀነሱን ጠቅሶ የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews