EthiopiaNews

የወሩ የዋጋ ግሽበት

የሚያዝያ ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን 11 ነጥብ 7 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል።

በተለይም የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 13 ነጥብ 5 በመቶ የጨመረ ሲሆን በዋናነት አትክልት፣ ስጋ፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመራቸው የተመዘገበ ጭማሪ መሆኑንንም ገልጿል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 9 ነጥብ 1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 13 በመቶ፣ በኮሙዩኒኬሽን 9 ነጥብ 7 በመቶ፣ የምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 10 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 15 ነጥብ 9 በመቶ ሆነው መመዝገባቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ይሀው የሚያዝያ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጭማሬ ያሳየ ሲሆን የመጋቢት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 9 ነጥብ 4 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አገልግሎቱ በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews