የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ
ናይጄሪያዊው ባለፀጋ አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ የ17 ቢሊየን ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት እቅድ መያዙ ተነገረ።
ዳንጎቴ ኩባንያ በኬንያ ለማስገንባት ያቀደው የነዳጅ ማጣሪያ በቀን 650 ሺ በርሜል የማጣራት አቅም እንዳለው ነው የተገለፀው።
የአፍሪካ ቁጥር 1 ባለሃብቱ አሊኮ ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያውን በኬንያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ ለማስገንባት ማቀዱን ገልጿል።
ኬንያ ትልቋ የምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗ እና ከፍተኛ የነዳጅ ምርት ተጠቃሚ ዜጎች ያላት በመሆኑ ምክንያት በዳንጎቴ ተመራጭ ሆናለች ተብሏል።
አሊኮ ዳንጎቴ አሁን ኳሷ በኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ እጅ መሆኗን ገልፆ ፕሬዚዳንቱ ካዘዙን ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ እንገባለን ብሏል።
ዘገባው የፋይናሺያል ታይምስ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
