EthiopiaNews

የፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ጉብኝት

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመጪው ረቡዕ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተነግሯል።

የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከትላንት በስትያ ቅዳሜ በግብፅ የጀመሩት ፕሬዝዳንቱ ዛሬ እና ነገ በኬንያ በመጪው ረቡዕ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንደሚያደርጉም የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ይህ ጉብኝት ፈረንሳይ በበርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ያጣችውን ድጋፍ መልሳ ለማግኘትና ተፅዕኖዋን እንደገና ለመገንባት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ተብሏል።

ፈረንሳይ ትኩረቷን ወደ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት፣ የንግድ ስምምነቶች፣ ቴክኖሎጂ፣ መሰረተ ልማት እና ዲፕሎማሲ እያዞረች ስለመሆኑ እንዲሁ የተገለፀ ሲሆን ማክሮን በናይሮቢ በሚካሄደው “አፍሪካ ፎርዋርድ” በተሰኘው ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ምክክር እንደሚያደርጉና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ስለ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይመክራሉ ነው የተባለው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv