የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ስምምነት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ቋሚ የሁለትዮሽ ምክክር ማዕቀፍ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታወቀ።
ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ እና የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊሰን ሁከር በዋሽንግተን ዲሲ ፈርመዋል።
በዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ የሚያጠናክሩ የጋራ ትግበራ የሚሹ የትብብር አድማሶችን በማስፋት በሁለትዮሽ ፣ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
የተፈረመው የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ምክክር በየዓመቱ አንዴ አዲስ አበባ ሌላ ጊዜ ዋሽንግተን የሚካሄድ ሲሆን የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባውን በጋራ የሚመሩት ይሆናል።
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሹ መዋቅራዊ ምክክር ሦስት ምሰሶዎችን ያካተተ እንዲሆን ተስማምተዋል።
ስምምነቱ ካካተታቸው 3ቱ ምሰሶዎች ውስጥ አንደኛው የኢኮኖሚ እድገት ፣ንግድ እና ኢንቨስትመንት ሲሆን ሁለተኛው የመከላከያ እና ጸጥታ ትብብር እና ሦስተኛው ምሰሶ ደግሞ ቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋትን የተመለከተ ነው ተብሏል።
መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
