የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ጋር በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው መምከራቸውን ተናገሩ።
ማርኮ ሩቢዮ ይሄን ያሉት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ የጋራ ጉባኤ ላይ ነው።
የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት በሀገራቱ የጋራ የፀጥታ ትብብር እና በንግድ እድሎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ማርኮ ሩቢዮ በምስራቅ አፍሪካ የሚስተዋለው ግጭት እንዲረግብ እና ቀጠናዊ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ የኢትዮጵያ ሚና ወሳኝ ነው ማለታቸውን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
መረጃው ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
