EthiopiaNews

ከስደት ተመላሽ ዜጎች

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺ 612 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሰቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

‌‎ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 229 ወንዶችና 383 ሴቶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 134 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።

‎መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል ነው የተባለው።

‎ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

‎በተጨማሪም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር እየተከናወነ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv