InternationalNews

የእስራኤል ጥቃት በሊባኖስ

🔸እስራኤል ትላንት በደቡብ ሊባኖስ በፈፀመችው ጥቃት በትንሹ 13 የአካባቢው ነዋሪዎች ተገደሉ።

🔸ከትላንቱ ጥቃት ከአንድ ቀን በፊት እስራኤል በናቤቴ ከተማ በፈፀመችው ጥቃት የተጐዱ ነዋሪዎችን ነፍስ ለማዳን የተሰማሩ እርዳታ ሰራተኞችም ተገድለዋል።

🔸የቤይሩት መንግስት በቅርቡ የተኩስ አቁም ከተደረገ በኋላ 380 ዜጐቿ በተጠናከረው የእስራኤል የአየር ድብደባ መገደላቸውን ይገልፃል።

🔸በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሄዝቦላ መሪ ናይም ቃስም በፊናቸው ድርጅታቸው ጦርነቱ እስራኤልን ወደሚለበልብ የምድር ገሀነም እንቀይረዋለን እያሉ ነው።

🔸እስራኤል ዛሬ በፈፀመችው ጥቃትም ከቤይሩት ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ በሚያመራ አውራ ጐዳና ላይ የነበረ ተሽከርካሪን በሚሳኤል መታለች።

🔸ኤፍፒ እንደሚለው እስራኤል ጥቃቱን እንዲህ ያፋፋመችው ከቤይሩት ጋር የደረሰችው ተኩስ አቁም ባለበት ሁኔታ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews