EthiopiaNews

ደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን

በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በህንድ በተጀመረው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ከስብስባው ጎን ለጎን ከደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ሲሆን ሚኒስትሮቹ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት መስማማታቸው ተገልጿል።

ሚኒስትሩ ከዚሁ ስብሰባ ጎን ለጎን ከህንድ አቻቸው ጋር ተወያይተው የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተማምነናል ብለዋል።

የህንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv