የክትትል ቡድኖቹ ሪፖርት
🔸በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ስምሪት የተሰጣቸው የክትትል ቡድኖች በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ላይ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን እንዳረጋገጡ ቦርዱ አስታወቀ።
🔸ቦርዱ ይሄን ያለው በቦርዱ ሥምሪት የሰጣቸው የክትትል ቡድኖች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት ባቀረቡበት ጊዜ ነው።
🔸የክትትል ቡድኖች በሪፖርታቸው በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ላይ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን አረጋግጠው አሁንም ትኩረት የሚሹ ቦታዎች መኖራቸውን ገልፀዋል።
🔸በሪፖርቱም ከፀጥታ ሁኔታ በተጨማሪ የየአካባቢዎቹ የፖለቲካ ምኅዳር፣ ፓርቲዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው የምርጫ ሥራቸውን ለመሥራት ምን ያኽል አስቻይ ሁኔታ አለ የሚለውን፣ ለምርጫው ያለው የሕዝብ ተነሣሽነትና የምርጫ ካርድ አወሳሰድ ሁኔታን ጨምሮ በርካታ የምርጫ ነክ ጉዳዮች ተዳሰውበታል።
👉መረጃው ከብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።
