ህገ-ወጥ የአክስዮን ሽያጭ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በትግራይ ክልል ከተሞች የሚንቀሳቀሰው ገዛና ጠቅላላ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር የተባለ ድርጅት የሚሽጣቸው አክሲዮኖች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡ መሆኑን አውቆ ማህበረሰቡ ከመግዛት እንዲቆጠብ አሳሰበ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገዛና ጠቅላላ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር በባለስልጣኑ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን በክልሉ በ4 ከተሞች ለሽያጭ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ይሄው ገዛና የተባለው ድርጅት ከባለስልጣኑ ማግኘት የሚገባውን የቅድመ ማስታወቂያ ፈቃድ ሳያገኝ በተለየዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ላይ የሚገኝ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በባለስልጣኑ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለሽያጭ ማቅረብ እንዲሁም የሽያጭ ማስታወቂያዎችን ማሰራጨት በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑን ያስታወሰው ባለስልጣኑ በአክሲዮን ማህበሩ ላይ የተጀመረው አስተዳደራዊ ምርመራ የሚቀጥል መሆኑንም ገልጿል፡፡
አክሎም ህብረተሰቡ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ከመግዛት እንዲቆጠብ እና ለማንኛውም የሽያጭ ወኪልም ሆነ ለአክሲዮን ማህበሩ ክፍያ እንዳይፈጽም በጥብቅ አሳስቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
