EthiopiaNews

ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎች

🔸የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 760 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታወቀ፡፡
‎
🔸‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 251 ወንዶች እና 460 ሴቶች እንዲሁም 49 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 38 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
‎
🔸‎ሚነስቴሩ መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ74 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ገልጿል።
‎
🔸‎ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews