EthiopiaNews

በጥሞና ወቅት የተከለከሉ ድርጊቶች

🇪🇹 የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ምርጫው እለት ያሉት ቀናት የጥሞና ቀናት መሆናቸውን ገልፆ የተከለከሉ ድርጊቶችን ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት እንደሚያረጋግጥ ፣መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል ብሏል።

🇪🇹በጥሞና ወቅት ምን ምን ማድረግ አይቻልም??

  1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች
    🚫 ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
    🚫   የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
    🚫   የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
    🚫  የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ

  2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
    🚫የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
    🚫   የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
    🚫  ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ

መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews