InternationalNews

ጋዛን የመቆጣጠር ትእዛዝ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገራቸው ጦር በጋዛ የተቆጣጠረውን ይዞታ ወደ 70 በመቶ እንዲያሳድግ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ሀገራቸው የጋዛ ሰርጥን 60 በመቶ መቆጣጠሯን በገለጹበት አንድ መድረክ ላይ ሀማስን መውጫና መግቢያ ለማሳጣት አሁን ላይ የእስራኤል ጦር ጋዛን 70 በመቶ እንዲቆጣጠር ማዘዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሀማስን በሁሉም አቅጣጫ ከበባ ውስጥ እያስገቡ መሆናቸውን የተናገሩት ኔታንያሁ ቀስ በቀስ የጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ቡድኑን ለማስወገድ እንደሚሰራም መጠቆማቸው ነው የተመለከተው፡፡

ሆኖም መሰሉ የእስራኤል እርምጃ በእስራኤልና በሀማስ መካከል ባለፈው ዓመት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት የሚቃረን መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv