EthiopiaNews

የምርጫ ዝግጅት መጠናቀቅ

የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 47 ተፎካካሪ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በ19 ዙር ክርክር ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ መራጩ ህዝብ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሚሰጠው ድምፅ ወኪሎቹን በዕውቀት ላይ መስርቶ እንዲመርጥ ለማስቻል የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሕብረትንና ኢጋድን ጨምሮ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች በሚሳተፉበት በዚህ ምርጫ ላይ ለመታዘብ 16 የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የመጎብኘት ጥያቄ ማቅረባቸውን የጠቀሱት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ምላሽ ለመስጠት በሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv