EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ቅርሶች

ነዋሪነታቸው በሮም የሆነው ጣሊያናዊው ሚስተር ሎሬንዞ ቦሲ ከረጅም ዓመታት በፊት በቤተሰቦቻቸው የተሰባሰቡ የኢትዮጵያ ሀይማኖታዊ ቅርሶች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በሮም ለሚገኘው ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አሳወቀ።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ቅርሶቹ የኢትዮጵያ ስለመሆናቸውና አለመሆናቸው እንዲሁም ጥንታዊነታቸውና ታሪካዊነታቸውን እንዲሁም የቅርሶቹን ፎቶግራፍ በጥልቅ መርመሩንም ገልጿል።

በምርመራውም በሎሬንዞ ቦሲ በኩል የተመለሱ መስቀሎች በትክክል የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ዕደ ጥበባዊ ቅርሶች መሆናቸውንም እንዳረጋገጠም ነው ባወጣው መግለጫ የጠቀሰው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv