የሱዳን የሰላም ድርድር
የሱዳን የፖለቲካ እና ሲቪል ሀይሎች የሱዳንን ጦርነት ማስቆም የሚያስችል የሰላም ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል።
በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየውን ይህንን ውይይት አስመልክቶ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ ውይይት በሱዳን ሰላም ማምጣት የሚያስችል ፖለቲካዊ ሂደት በቀጣይ ለመጀመር የሚያስችል ግብዓት መገኘቱ ነው የተነገረው።
ይህንን ውይይት ተመድ፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአረብ ሊግ እና ኢጋድ በጋራ በመተባበር ማዘጋጀታቸው ተሰምቷል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
