የመምህሩ ረዳት ኤአይ መተግበሪያ
ትምህርት ሚኒስቴር የመምህር ረዳት የሆነ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ የዋለው የኤ አይ መተግበሪያው የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና በእጅጉ የሚቀንስ፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ እና ራሱን ችሎ ተግባራትን የሚያከናውን ነው ብሏል።
ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” የተሰኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ ቴክኖሎጂ ላይ የማይተማመን እና በአካባቢያዊ ኮምፒውተር ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሰራ ነው ተብሏል።
መተግበሪያው የትምህርት እቅድ ያዘጋጃል፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን ያመነጫል፣ እንዲሁም ማስተማሪያ ስልቶችን በራሱ ማቀናጀት ይችላል።
መተግበሪያው መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ቀጥታ ለሚኖራቸው ግንኙነት በቂ ጊዜ እንዲያገኙ ከመርዳቱም ባሻገር፣ የመምህራንን የማስተማር ብቃትና አቅም ስለሚያጎለብት የትምህርትን ጥራት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ሚነስቴሩ ገልጿል።
መተግበሪያው በተለየ ሁኔታ የኢንተርኔት ኔትወርክ በሌላቸው ወይም በጣም ውስን በሆነባቸው የገጠርና ራቅ ያሉ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለምንም መቆራረጥ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል። መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
