EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መኖሪያቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመር ሳያስፈልጋቸው በጊዜያዊነት በልዩ ሁኔታ መስተናገድ የሚችሉበትን አሠራር መዘርጋቱን ገልጿል።

የመኖሪያ አድራሻቸው ከኢትዮጵያ ውጭ ሆኖ የባንክ ሂሳብ ጋር ያላጣመሩ እና ማስረጃ ያቀረቡ ደንበኞች ሂሳብ አለመታገዱን ነው ባንኩ ባወጣው መግለጫ የገለፀው።

ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ውጭ ሀገር እንደሚኖሩ በባንኩ የመረጃ ቋት ላይ ያላስመዘገቡ እና የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች ከኢትዮጵያ ውጭ መኖራቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ እግዱ የሚነሳ መሆኑንም ባንኩ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv