አዲሱ የግብር ከፋዮች ምደባ
የገቢዎች ሚኒስቴር አዲሱ የግብር ከፋዮች ምደባ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገለጸ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን የገለጸው የ2019 በጀት ዓመት የታክስ ከፋዮች የደረጃ ምደባ ኮሚቴ ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለበላይ የስራ ሃላፊዎች ባቀረበው ሪፖርት ላይ ነው፡፡
በዚህ ወቅት የገቢዎች ሚኒስትሯ ዓይናለም ንጉሴ የምደባው ዓላማ ግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ተደራሽነት ለማስፋት እንዲሁም የግብር ከፋዮችን አደረጃጀት ለማስፋት ታስቦ ነው ብለዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች የደረጃ ምደባ የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን መሠረት አድርጎ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
