በሚቀጥሉት 10 ቀናት በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብና እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት አስታውቋል።
ኢንስቲትዮቱ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጥል የገለጸ ሲሆን ከፍተኛ የፀሐይ ኃይልን ተከትሎ በአፋር፣ በሰሜን፣ በምዕራብና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሊደርስ እንደሚችልም ጠቁሟል።
በተጨማሪም አብዛኛው የአባይ፣ ባሮ አኮቦ፣ ኦሞ ጊቤና የላይኛው ስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ወንዞች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖር ኢንስቲትዮቱ በአሃዛዊ የትንበያ መረጃው አመልክቷል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
