EthiopiaNews

የአለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 ሚሊየን በላይ አፍሪካውያን ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ማድረጉን አስታወቀ።

የአለም ባንክ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ሚሽን 300 በተባለው መርሃግብራቸው በኩል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 ሚሊየን በላይ አፍሪካውያን ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ተቋማቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ ባለፉት 2 አመታት በተተገበረው ሚሽን 300 በተሰኘው መርሃግብር በኢትዮጵያ ብቻ 4.6 ሚሊየን ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መርሃግብሩ በ40 የአፍሪካ ሀገራት መተግበሩን እና ከ50 ሚሊየን በላይ ሰዎችም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ችለዋል ተብሏል።

ይሄው መርሃግብር በታንዛኒያ 7.5 ሚሊየን እና በናይጄሪያ 4.5 ሚሊዮን ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል ተብሏል።

መርሃግብሩ በፈረንጆቹ 2030 አመት 3መቶ ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱ ነው የተገለፀው፡፡ መረጃው ከአለም ባንክ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews