የአፍሪካ ኅብረት ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለተደረገው ጥረት እውቅና አንደሚሰጥ ገልጿል።
የአፍሪካ ኅብረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግስትና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላደረጉት ጥረት እውቅና አንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ቡድን በማሰማራት ምርጫውን መታዘቡን የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የተመራ የኅብረቱ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የመጀመሪያ ዙር ሪፖርት ማቅረቡን አስታውሰው ምርጫው ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ታሪካዊ መሰረት ነው ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የዴሞከራሲ ስርዓትና የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲጠናክሩ እንዲሁም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር የአፍሪካ ኅብረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል፡፡
አፍሪካ ዴሞክራሲን ከመለማመድ ውጭ አማራጭ እንደሌላት የገለጹት ኮሚሽነሩ በአህጉሪቱ ቅቡልነት ያለው የመንግስታት ምስረታ እንዲከናወን በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
