EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው የአውሮፕላን አምራች ዲ ሃቪላንድ ኩባንያ ካዘዛቸው ዘመናዊ የዲ.ኤች.ሲ-6 ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያውን መረከቡን አስታወቀ።

እነዚህ ልዩ አውሮፕላኖች የአየር መንገዱን የቀጠና አገልግሎት ያጠናክራሉ ያለው ኩባንያው፣ አውሮፕላኖቹ አስቸጋሪ በኾኑ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦች ውስጥ በቀላሉ መብረር የሚችሉ በመኾናቸው ለቱሪዝም፣ ለአየር ላይ ቅኝቶች፣ ለጤና አገልግሎቶች እና ለሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው ገልጿል። መረጃው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews