Sports

EBS SPORT- ክሮሺያ ብራዚልን በመርታት ለግማሽ ፍፃሜ ደርሳለች

🇭🇷 ክሮሺያ ብራዚልን በመለያ ምት በመርታት በታሪኳ ለሶስተኛ ጊዜ ግማሽ ፍፃሜ ደርሳለች። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመደበኛው ሰዓት 0ለ0 የተጠናቀቀ ሲሆን የተጨመረው 30 ደቂቃ 1ለ1 መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርቷል። በመለያ ምቱም ክሮሺያ 4ለ2 በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።ሃገሪቱ ብራዚልን ስታሸንፍ የመጀመሪያዋ ነው። ሴሌሳኦቹን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ኔይማር ከመረብ ሲያሳርፍ አውሮፖዊቷን ሃገር ወደ መለያ ምት ያሸጋገረችውን ግብ ፔትኮቪች በ117ተኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። ኔይማር በ77 ግቦች የብራዚል የምንግዜም ከፍተኛ አሰቆጣሪነት ክብረወሰንን ከፔሌ ጋር ተጋርቷል ።ክሮሺያ በአለም ዋንጫው ወደ መለያ ምት የደረሰችባቸውን አራቱንም ጨዋታዎች በአሸናፊነት አጠናቃለች። በ1992 የሃገራት ደረጃ በፊፋ ይፋ መሆን ከጀመረ ጀምሮ ከውድድሩ መጀመር በፊት በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጠ አንድም ሃገር ሻምፒዮን መሆን አልቻለም።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New