EthiopiaNews

ስለ ለኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በኩዌት

የኩዌት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን ጨምሮ የ10 ሀገራት የቤት ሰራተኞች በሀገሪቱ እንዲቀጠሩ የሚፈቅድ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።

የኩዌት መንግስት ይሄን ያለው 24 የአፍሪካ ሀገራት እና ሁለት የእስያ ሀገራት የቤት ሰራተኞች በኩዌት እንዳይቀጠሩ የሚያግደውን መመሪያ ይፋ ባደረገበት መግለጫ ላይ ነው።

መመሪያው ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ፊሊፒንስ ጨምሮ የ10 ሀገራት የቤት ሰራተኞች በኩዌት እንዲሰሩ የሚፈቅድ መሆኑን ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ዘግቧል።

ይህ አዲስ መመሪያ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር እና የሰው ኃይል ባለስልጣን ባቀረቡት ምክረ-ሀሳብ ላይ ተመስርቶ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ተገልጿል።

የሰራተኞች ቅጥር ሂደቱን የኩዌት መንግሥት በጥብቅ እንደሚቆጣጠረው በዘገባው ተመልክቷል።