በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሌልቱ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነችውን አዳነች ኩምሳን ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ፀጋዬ አሳልፈው ጎንጤ የተባለው ተጠርጣሪ በደብረ ብርሃን ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አሳውቋል።
ሟች እና ተጠርጣሪ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በምሽት በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በመካከላቸው አለመግባት በመፈጠሩ ሟች ተጠርጣሪውን ጥላ በመሄዷ ተከትሏት ወደ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ”ጎማጣ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሽጉጥ ተኩሶ ገድሏት ጥሎ በመጥፋቱ የሟች አስክሬን በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ መገኘቱን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያመላክታል።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን የፈጸመበትን መኪና እና ሽጉጥ በአሌልቱ ከተማ ጥሎ መሰወሩን የደረሰበት ፖሊስ በመኪናው ውስጥ የደም ዱካ እና ሽጉጡን እንደ ማስረጃ በመጠቀም ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪው የተለያዩ ሐሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣት በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢት እና በአጣዬ ከተሞች ሰላማዊ ሰው መስሎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልፆ ትናንት በደብረ ብርሃን ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን ይፋ አድርጓል።
መረጃው ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
