EthiopiaNews

በበጀት ዓመቱ በመዲናዋ ውስጥ ከሚገኙ 2025 ፕሮጀክቶች 920 ያህሉ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ በ2018 በጀት ዓመት ከቀረቡ በተለያዩ ተቋማትና ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ 2025 ፕሮጀክቶች ውስጥ 920ው ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደበቁ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ አሳወቀ፡፡

በፕሮጀክቶቹ ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረጉን የገለጸው ቢሮው ከእነዚህ መካከል
ባለፉት 11 ወራት ከተቋረጡ ፕሮጀክቶች ለመንግስት መመለስ ከነበረበት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በክፍለ ከተማ እና በማዕከል ደረጃ በድምሩ ከ435 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም 8 ሚሊዮን የሚጠጋ ዩሮ ለመንግስት ተመላሽ መደረጉንም ገልጿል፡፡

በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ 304 ፕሮጀክቶች እንደሚገኙም የተጠቆመ ሲሆን ቀሪዎቹ 801 ፕሮጀክቶች ደግሞ በማህበራት አማካኝነት የሚከናወኑ የአረንጓዴ ልማትና የእንክብካቤ ሥራዎች ናቸው ተብሏል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews