EthiopiaNews

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ተነገረ።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት አስታወቀ።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ቀደም ሲል ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓም እንደሚሰጥ ቢገለጽም፤ ከትምህርት ባለድርሻዎች ጋር በተደረገ ውይይት ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲሰጥ መወሰኑን ነው አገልግሎቱ ያሳወቀው።

ለፈተና ከተመዘገቡት ከ563 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከል 306 ሺህ ያህሉ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ 257 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በማኅበራዊ ሳይንስ ለፈተናው እየተዘጋጁ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፈተናው በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሀረር ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል፡፡

የመሠረተ ልማት ግንባታ ባልተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች የኦን ላየን ተፈታኞች ቁጥሩ ከፍ ዝቅ ሊል እንደሚችልና ወደ ወረቀት ፈተና ሊመለስ እንደሚችል የጠቆመው አገልግሎቱ ፈተናው የተፈጥሮ ሳይንስ ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 3 ቀን፤ የማኅበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ ሐምሌ 16 ቀን እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews