EthiopiaNews

በአ.አ ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ለመወሰን የሚያስችል ጥናት መደረጉ ተገለጸ።

በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የሚስተዋሉ ህገወጥ አሰራሮችን መፍታትና የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ለመወሰን የሚያስችል ጥናት ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መወሰኛ ጥናት ላይ ከባድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ያካሄደ ሲሆን ጥናቱ አከራይ ከንብረቱ ተገቢውንና የወቅቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኝ የሚያደርግ ነውም ብሏል።

እንዲሁም ተከራዩ ከገቢው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ከማገዝ በተጨማሪ ገበያውን ጤናማ በማድረግ የንግድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማረጋጋት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረውም ጠቅሷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews