InternationalNews

አሜሪካና ኢራን በመካከላቸው ያለውን ግጭት ማስቆም በሚያስችለው የስምምነት ማዕቀፍ ላይ መስማማታቸው ተገለፀ።

ሁለቱን ሀገራት ስታሸማግል የቆየችው ፓኪስታን አሜሪካና ኢራን በዚህ የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ ላይ የፊታችን ዓርብ በአውሮፓዊቷ ስዊዘርላንድ እንደሚፈራረሙ ነው ያሳወቀችው፡፡

የዚህን ስምምነት መደረስ አስመልክቶ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ በለጠፉት መልዕክት ኢራን ከስምምነት ላይ መድረሷን ጠቁመው የሆርሙዝ ሰርጥ ይከፈታል ነዳጁም እንደከዚህ ቀደሙ ይፈሳል ሲሉ ስምምነቱን አዳንቀዋል፡፡

የኢራን ምክትል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ከስምምነት ላይ መደርሷን ያረጋገጡ ሲሆን የኢራን አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር በበኩላቸው ስምምነቱ ለኢራን ትልቅ ድል  መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv