አዲሱ የሰላም ዕቅድ
ኢራን የአሜሪካን አዲሱን የሰላም ዕቅድ እያጤነችበት መሆኑን አሳውቃለች።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፊናቸው የኢራን ጦርነት በአስቸኳይ እንደሚቆም ያላቸውን ተስፋ ጠቁመው በርካታ ሰዎችም የኢራንን የኒውክለር ጦር መሣሪያ ባለቤትነት ህልም ማክሸፍን የተመለከተውን ዓላማቸውን እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡
የቢቢሲ ዘገባ እንደሚያመለክተው አሜሪካ ያቀረበችውን ባለ 14 ነጥቦች የመግባቢያ ስምምነት ኢራን ትቀበላለች የሚል ተስፋ ያጫረች ሲሆን ይህም ስምምነት በሀገሪቱ የኒውክለር ፕሮግራም ዙሪያ በዝርዝር መነጋገር የሚቻልበትን ማዕቀፍ ያበጃል ተብሏል፡፡
የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የመግባቢያ ስምምነቱን በተመለከተ የቴህራንን አቋም ለአሸማጋይዋ ፓኪስታን እንደሚያስረክቡ ሲገልጹ አንድ ኢራን ፓርላማ አባል ደግሞ መግባቢያ ስምምነቱን ፍፁም ቅዠት ሲሉ አጣጥለውታል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
