News

አዲስ ነገር – ሽልማት ለአዲስ አበባ

አዲስ አበባ ከተማ እያከናወነችው ባለችው የትምህርት ቤቶች የምገባ መርሀ ግብር በብራዚል በተከናወነ አንድ ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ተሸላሚ ሆነች።ሚላን አርባን ፎድ ፖሊሲ ፓክት የተሰኘና በዓለም አቀፍ ደረጃ የከተማ ምግባና ምግብ ነክ ስራዎች ላይ በተለያየ መልኩ የሚሰራው ተቋሙ በየዓመቱ በምግብ ስርዓታቸው ለሌሎች ተሞክሮ ይሆናሉ ያላቸውን ሀገራት በ6 ዘርፍ ይሸልማል።በዚህም መሰረት ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ ባከናወነው የሽልማት መርሀ ግብር አዲስ አበባ እያከናወነች ባለው የተማሪዎች ምገባ መርሀ ግብር ዘላቂ አመጋገብና ስነ ምግብ በሚል ዘርፍ ከተወዳደሩ 133 ከተሞች ቀዳሚነት ናት በማለት እውቅና እንደሰጣት ነው የተሰማው። በከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው ልዑክም ወደ ብራዚሏ ሪዮ ዲጀነሪዮ በማቅናት ሽልማቱን መረከቡን ከከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New