News

አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇨🇳#ቻይና ቻይና እና ሳኡዲ አረቢያ 34 የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ተፈራረሙ።በሳኡዲ አረቢያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ጉብኝት ተከትሎ ነው ቤጂንግ እና ሪያድ በ34 የኢንቨስትመንት ዘርፎች አብረው ለመስራት ስምምነት የተፈራረሙት ።ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ በሪያድ በተሰናዳው የቻይና አረብ አገራት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ሳኡዲ አረቢያ እና ቻይና በፈረንጆቹ 2021 የነበራቸው አመታዊ የንግድ ልውውጥ 80 ቢሊየን ዶላር እንደነበር አል አረቢያ በዘገባው አመልክቷል።

🇷🇺#ሩሲያ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን እየተካሄደ ያለዉ ወታደራዊ ዘመቻ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድ ተናገሩ።ፕሬዝዳንት ፑቲን ይሄን ያሉት በዩክሬን ጦርነት የክሬምሊን መንግስት የማይካድ ድል መጎናፀፉን ባስታወቁበት ጊዜ ነው ።ፕሬዝዳንቱ በዩክሬን ለሚካሄደው ጦርነት ተጨማሪ ወታደሮች ምልመላ አያስፈልገንም ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

🇺🇬#ኡጋንዳ ኡጋንዳ በሙከራ ደረጃ ላይ ያለውን የኢቦላ ክትባት መረከቧን አስታወቀች ።በኢቦላ ወረርሽኝ ተጐድታ የነበረው ኡጋንዳ 1200 ብልቃጥ በሙከራ ላይ ያለ የኢቦላ ክትባት መረከቧን ሲነገር የኢቦላ ክትባቱ በቫይረሱ ለተያዙ ዜጐች በቀናት ውስጥ የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።በኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ ስርጭት ረገብ ቢልም በቫይረሱ 55 ሰዎች ሞተው 142 ዜጐች ደግሞ በኢቦላ መያዛቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New