News

አዲስ ነገር – የዲጂታል ትምህርት ማዕከላት

ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ያለውን የዲጂታል ትምህርት ማዕከል ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል፡፡
ኩባንያው ከሰዓታት በፊት ይፋ ያደረገው ፕሮጀክት ከዚህ በፊት የመሠረተ ልማት ችግር በነበረባቸው በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 48 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም በአዲስ አበባም በ18 ትምህርት ቤቶች የሚተገበር ነው ብሏል፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂን አውቀው ቢያድጉ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ የሚለው ኩባንያው ለዚህም በፕሮጀክቱ አማካኝነት ለትምህርት ቤቶቹ የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የትምህርትመሠረተ ልማቶች ማሟላቱን አሳውቋል፡፡
አሁን ይፋ ያደረኩት የዲጂታል ትምህርት ማዕከል ፕሮጀክት በጥቅሉ 140 ሺህ 596 ተማሪዎችን የሚጠቅም መሆኑንም እወቁልኝ ብሏል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New