ኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ዶላር የነበረውን የዩሮቦንድ ዋጋ የ12 በመቶ ቅናሽ እንዲደረግበት የሚያስችል ስምምነት ላይ ደረሰች፡፡
ኢትዮጵያ እና የግል አበዳሪዎች ኮሚቴ ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲያካሂዱ የቆዩት የአንድ ቢሊዮን ዶላር ቦንድ የዕዳ ሽግሽግ ድርድር በስምምነት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
በእነዚህ ቀናት በተደረገው ንግግር የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መደረሱን የገለጸው የገንዘብ ሚኒስቴር በዚህ ስምምነት መሠረት 1 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የቦንዱ ዋጋ የ12 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት ለባለሀብቶቹ የሚመለስላቸው ገንዘብ 880 ሚሊዮን ዶላር እንዲሆን የሚያደርግ ነው።
ይህ የቦንዱ ዋጋም እስከ ሐምሌ 2021 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በአራት ክፍያ የሚፈጸም ሲሆን ቦንዱ ተከፍሎ እስከሚጠናቀቅበት 2021 ዓ.ም ድረስም ኢትዮጵያ የ6 ነጥብ 15 በመቶ ወለድ እንድትከፍል የሚያደርግ ነው፡፡
ይህ አዲስ ስምምነት ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ቀርቦ የተገመገመ መሆኑን የጠቀሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ወደፊት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ለሽያጭ በምታቀርብበት ጊዜ እኚሁ ባለሀብቶች ድርሻ እንዲገዙ መብት የሚሰጣቸው አማራጭ ያካተተ መሆኑም ጠቅሷል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
