EthiopiaNews

ከሳኡዲ ተመላሽ ዜጎች

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 439 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን አስታወቀ።
‎
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 7 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 380 ወንዶች እና 57 ሴቶች እንዲሁም 2 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 49ኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
‎
‎ሚኒስቴሩ ያለፈው መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ67 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
‎
‎
መረጃው ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv