የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ አቀረበ።
የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ በፈተና አስተዳደር ሲስተም ላይ (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን አገልግሎቱ ገልጿል።
አገልግሎቱ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ገልጾ ተፈታኝ ተማሪዎች የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው እንዲወስዱ አሳስቧል።
ተፈታኞች በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ፣ የጾታ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት እንዲያስተካክሉ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።
ተፈታኞች በፈተና ወቅት ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
