EthiopiaNews

የመንግስት ተቋማት ንብረት አወጋገድ

በመንግስት ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ኬሚካሎች በወቅቱና በስርዓቱ እንደማይወገዱ የፌደራል የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በ26 የፌዴራል ተቋማት ንብረት አወጋገድ ስርዓት ዙሪያ ይፋ ባደረገው ጥናት ህጋዊ አሰራርን ሳይከተሉ ንብረቶች እንደሚወገዱ፣ የሚወገዱ ንብረቶች አቀማመጥ በንብረቶቹ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንና በግዥ የሚቀርቡ እቃዎች ላይ ተገቢ ቁጥጥር እንደማይደረግ አመልክቷል፡፡

እንዲሁም የሚወገዱ ንብረቶች ከአዳዲስ ንብረቶች ጋር ተቀላቅለው እንደሚቀመጡና በግዥ የሚቀርቡ እቃዎች ላይ ተገቢ ቁጥጥር እንደማይደረግ ያመለከተው ጥናቱ የንብረት አወጋገድ ክትትልና ቁጥጥሩ ጠንካራ አለመሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፍቃዱ ሆሮታና ሰመሪታ ሰዋሰውን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በቀረበው ጥናት ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች የፌደራል የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ምክትል ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሙስና የሚሳተፋ ግለሰቦችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥም ከፌደራል ፖሊስና ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሆነም ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews