የሚድሮክ እና የአይኤፍሲ ስምምነት
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ወይም በምህፃረ ቃሉ አይ ኤፍሲ የ80 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የአፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮጲስ ተፈራ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሰረት ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 80 ሚሊዮን ዶላር የረዥም ጊዜ ብድር ያቀርባል።
በተገኘው ገንዘብ ደግሞ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴልን በዘመናዊ መልኩ እንደሚያድስ እና በሸራተን ደረጃ አዲስ ሆቴል እንደሚገነባ ነው የተገለፀው።
ጀማል አሕመድ ከአይ ኤፍሲ ጋር የተጀመረው አጋርነት የሀገሪቱን የሆቴል ዘርፍ እንደሚያዘምን እና የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናገረዋል።መረጃው ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
