EthiopiaNews

አዲሱ የግሪክ የስደተኞች ህግ

የግሪክ ፓርላማ ሀገሪቱ ስደተኞችን በፍጥነት ወደየመጡበት ሀገር መመለስና በሶስተኛ ሀገራት ማስፈር የሚያስችላትን ሕግ ማፅደቁ ተሰምቷል፡፡

በዚህ ህግ መሰረት ጥገኝነት ጠይቀው ጥያቄያቸው ውድቅ የሚደረግባቸው ስደተኞች ከግሪክ በአስቸኳይ የሚባረሩ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር ካልሆኑ ሀገራት ጋር በሚደረግ የሁለትዮሽ ስምምነትም ወደ ሶስተኛ ሀገራት ይባረራሉ ነው የተባለው፡፡

ግሪክ ለአፍሪካ በጣም ቅርበት ያላቸው ሁለት ደሴቶች ያሏት መሆኑን ተከትሎ እንደሊቢያ ካሉ ሀገራት በሚመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች እየተፈተነች መሆኑን የሚጠቁመው የሮይተርስ ዘገባ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ይህ ችግር ተባብሷል፡፡

የአውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ ሀገራት ማባረር የሚያስችለውን አዲስ ህግ በቅርቡ ማፅደቁ የሚታወስ ሲሆን ግሪክ ስደተኞችን በዩጋንዳ ለማስፈር ከሀገሪቱ መንግስት ጋር እየተነጋገረ መሆኑም ተመለክቷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv